Email the Author
You can use this page to email ኢትዮጵያ about ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ከጳውሎስ ኞኞ.
About the Book
ጠቅላላውን የኢትዮጵያ ታሪክ ስንመለከት የኢትዮጵያ ነገሥታት ሁሉ በየዘመናቸው የየዘመኑን የውጭ ጥበብ ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ያልተመኘ ንጉሥ የለም። አብዛኛዎቹም ከውጭ አገር የሚጠይቁት ጥበባዊ ሥራ የጥይት የመድፍ መሥሪያ ነው። ይህም ከውጭ የሚመጣውን ጠላት ለመከላከል ወይም ደግሞ ያገር ውስጥ ተቀናቃኙን ለመደምሰሻ ነው።
ምኒልክ በጦር መሣሪያ ፍለጋ ብቻ የተገቱ ሳይሆኑ በዘመናቸው በውጭ አገር የነበረውን ጥበባዊ ሥራ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡ ሰው ናቸው። አሁን በአገራችን የምናየው ወይም የምገለገልበት በኋለኛው ዘመን ከተፈለሰፉት አዳዲስ ግኝቶች በስተቀር በምኒልክ ጥረትና ዘመነ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው። እነኚህንም ጥንታዊ ሥልጣኔዎችን ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ምኒልክ ምን ያህል ችግርና ፈተና ደርሶባቸው እንደነበር ከመጽሐፉ ውስጥ ገባ ስንል እናገኘዋለን። ምኒልክ ያን ሁሉ ችግር የለፉና ኢትዮጵን መሥርተው በእግርዋ ያቆሙ ሰው ናቸው።
- ጳውሎስ ኞኞ
About the Author